Frequently Asked Question

በደንበኞች የሚነሱ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

ሐሰንያስ ወደ ሪል እስቴት በገባበት አጭር /5 ዓመታት/ ውስጥ እያሳየ ያለው ዕድገትና መሻሻል የሚያበረታታ ነው፡፡ በግንባታው በኩልም ከተጀመረ ግዜ አንስቶ የሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ መልካም ነው፡፡ የቤቶች ዋጋም ቢሆን በኢንዱስትሪው ካሉት አልሚዎች አንጻር ሲታይ ጥሩ እና ተመጣጣኝ የሚባል ነው፡፡ የሰው ሐይሉም ቢሆን ገበያው ውስጥ የተካበተ ልምድ አላቸው በሚባሉ ባለሙያዎች እና ምሁራን የተደራጀ ነው፡፡ የደንበኛ አገልግሎቱም ቢሆን ደንበኛን ባማከለ መልኩ ነው፡፡

አሁን ባለው ተጨባጭ የባንክ አሰራር ሒደት ባንኮች ብድር ለመስጠት የቤት ካርታ ፕላን ይፈልጋሉ፤ የሚመለከተው የመሬት አስተዳደር ካርታ አሰራር ሒደት የሚከናወነው ደግሞ የቤቱ ግንባታ 70 በመቶ ወይም ጣራ ከደረሰ በኋላ መሆኑ በቅድሚያ ብድሩን ለማግኘት አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን በእዚህ ሁኔታ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከእዚህ በተሻለ መስራት እንዳለብን እናምናለን፡፡

አንድ ውል የፈጸመ ደንበኛ ሁለት ዓይነት የክፍያ አካሔዶችን መምረጥ ይችላል፤ እነዚህም አንደኛው 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ፈጽሞ ቀሪውን 70 በመቶ በ24 ወራት ውስጥ በየወሩ ማጠናቀቅ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ቅደሚያ 30 በመቶ ከፍሎ ቀሪውን 70 በመቶ በ24 ወራት ውስጥ በግንባታው ቅደም ተከተል /20 በመቶ የመሰረት ስራ እንደተጠናቀቀ፣ 20 በመቶ የሱፐር እስትራክቸር ስራ እንደተጠናቀቀ፣ 10 በመቶ የጣሪያ እና የብሎኬት ስራ እንደተጠናቀቀ፣ 10 በመቶ የልስን ፣የአጥርና የሴፕቲ ታንክ ስራዎች እንደተጠናቀቀ እና 10 በመቶ ቤቱን ሲረከብ/ መሰረት ነው፡፡

በአሁን ሰዓት ሐሰንያስ ያለው ፕሮጀክት ‘አለምገና’ በሚገኘው 80,000 ካ.ሜ ላይ በሰፊው በተንጣለለው መንደር ላይ ነው፡፡ ይህ የሆነበትም ምክንያት በሙሉ ትኩረት እና ጥንቃቄ ለመስራት ከማሰብ አንጻር ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ግንባታ ወደ ማገባደጃው ሲደርስ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም ለመስራት የረዥም ግዜ ዕቅድ ውስጥ ተካቷል፡፡

አሁን ባለው የአገሪቷ ሕግ መሰረት አንድ ሰው ንብረት ሊኖረው የሚያስችልው አግባብ በዜግነት ኢትዮጵያዊ ከሆነ፣ በትውልድ ኢትዮጵያዊ ከሆነ፣ በጋብቻ ኢትጵያዊ ከሆነ እና የኢንቨስትመንት ፍቃድ ካለው ነው፡፡

The following are a general description of the structural methods to be incorporated in the property; Framework: The property is structurally supported by reinforced concrete founded on reinforced concrete footing, all of concreter class C-25; Building Blocks: Building blocks are class C Hollow Concrete Blocks, for 20 HLB external and 15 cm HLB internal except where otherwise provided for aesthetic purpose as shown on the drawings; Roof: the roof is an Alem Genet roof sheet, supported on treated eucalyptus trusses. & -16m X 5cm zigba or equivalent pinyin; Wall finishing: Internal wall shall be three coats of plastering & painted. & painted where color has to the chaise of the client. Leitto but Eternal wall cement plastered and quartz painted, Imported glazed Ceramic wall tile for kitchen , toilet (bath); Floor finishing: PVC floor for all bed rooms and living / dining room, Wooden flooring for landing , tread and riser, Ceramic floor tile for kitchen , toilet (bath ) & balcony; Ceiling: Gypsum board under roof, plastered and painted ; Main door: solid wooden; Internal Doors: semi- solid wooden; Cup-bored: it is not included in this sell contract, buyer may order for additional price to be agreed by then; Kitchen: semi – solid kitchen cabinet, marble top; Windows: imitation work Metal with 3mm thick clear glass with an option of aluminum; Frame with 6 mm tinted glass at the additional cost of the client By calculating an difference amount; High protection Grill: composite wooden & metal for interior and metal for exterior, Handrail of the stain case and balcony’s shall be supplied by Hassenias, Fence work shall be part of the contact (shale or alone), Ground floor tikes of the compound shall be part of the cushion , The courage or car port has to have roof cover on metal truss of column septic tank; Fences: PVC frame fence grill fixed on stone masonry wall .Metal RHS GRILL sliding main gate door; Walkways and parking: concrete tile around the building and car entrance; Electrical: Electric Fixtures chosen from a variety catalogue shall be supplied by heresies, Breakers, switches, sockets – La grande , Techno or equivalent; Sanitary: Fixtures are all ceramic except shower pro indicate the size of texture we peddisted mirror soap holder soft holder towel hanger has to be stated Modern kitchen since traditional. Trays and bath tubs, which are of steel cast iron pipes and valves mare HDPE.

የመኖሪያ መንደሩ ጠቅላላ ስፋት 80,000 ካ.ሜ. ሲሆን በውስጡ የተፈጥሮ ዕፅዋትን የያዘ፣ ወደ 10,000 ካ.ሜ. የመጫወቻ ስፍራ፣ የመዋኛ ስፍራ፣ ጂምናዚየም፣ በቂ የመኪና ማቆሚያ እና በደንብ ለጥበቃ ምቹ በሆነ መልኩ የተሰራ አጥር አለው፡፡

ዋጋችን በኢንደስትሪው ካሉ አልሚውች አንጸር ሲታይ በጣም ጥሩ የሚባል እና ከቤቱ ጋር የተመጣጠነ ነው፡፡ ይህ የሆነበትም ምክንያት መጀመሪያ ቢዝነሱን ስንጀምር ለታቀደው የደንበኞች ስብስብ /Target Group/ ተመጣጣኝ ዋጋ ከማቅረብ አንጻር ነው፡፡ ይህም ከሌሎች አልሚዎች እንድንመረጥ ከሚያደርገን ብዙ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡

የምንገነባቸው ቤቶች ዓይነት በዋናነት ቪላዎች /G+0 እና G+1/፣ ታውን ሐውሶች /G+1 በሁለት አቅጣጫ የተገናኙ የራሳቸው ግቢ ያላቸው ቤቶች/ እና ኮንዶሚኒየም አፓርትመንቶችን /G+4 በአንድ ወለል ላይ 4 አባወራ፣ በጠቅላላው በአንድ ሕንጻ ላይ 20 አባወራ የሚይዝ/ ነው፡፡

ሐሰንያስ የግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ንግድ እና ኮንስትራክሽን ድርጅት ከ15 ዓመት በፊት የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፤ ሪል እስቴቱ ደግሞ ከ5 ዓመት በፊት ተመስርቷል፡፡

የመጀመሪያው የሐሰንያስ ፕሮጀክት የሆነው በአለምገና ያለው መንደር በጠቅላላው ይህ ነው በሚል በአንዲት ውስን ቀን ይረከባል ለማለት ያስቸግራል፤ ምክንያቱም መጀመሪያ በመጣው ገዢ እና መጨረሻው ባለው ገዢ መካከል ባለው የግዜ ልዩነት ምክንያት ነው፡፡ ነገር ግን በተያዘላቸው ዙር መሰረት ርክክባቸው ከመጪው ዓመት 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ይጀመራል፡፡